ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡
ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡
ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡
በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡
በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡
ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡
ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡
በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡
በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡
ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡
ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡
በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡
ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡
የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡
መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡
ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡
እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡